Skip to content Skip to footer

Ed Lazere

ኤድ ለዚር

የዲሲ አጠቃላይ ምክር ቤት ዕጩ

ለዲሲ ቤተሰቦች በመታገል ስክታማነቱ የተረጋገጠ መሪ

ከኤድ ጋር ይተዋወቁ

ኤድ ላዘር ለኢኮኖሚ፤ ለዘረ ዕኩልነት እና ፍትህ ሲታገል የከረመ የዲሲ ነዋሪ ሲሆን፤ ሰፊ ልምድ ያለው ብቻ ሳይሆን—ስኬታማ መሪም ነው፤ ለረጅም ጊዜ ለተለያዩ ቅንጅቶች መሪ በመሆን ብቻ ሳይሆን የፓሊሲ እና የባጀት ባለሙያም ሆኖ ሲያገለግል ነው የከረመው፤ ሠራተኞች ተገቢ ክፍያ እንዲያገኙ፤ ነዋሪዎች አቅም የሚፈቀድ ቤት እንዲኖራቸው፤ የጤና እንክብካቤ ለሁሉም ተዳራሽ እንዲሆን፤ እና  ለሎች ተጨማሪ ጉዳዮች በከተማው ዙሪያ ካሉ የማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር አብሮ ሲሰራ ነው የቆየው፤ አሁን ደግሞ ቁርጠኝነት እና አርቆ አሳቢ መሪነት ወደ የሚያስፈልገው የዲሲ አጠቃላይ ምክር ቤት አባል ሆኖ ለመመረጥ እየተወዳደረ ይገኛል፡፡

ኤድ የፍታሃዊ ምርጫ ዕጩ ሆኖ በመቅረቡ ደስተኛ ነው፤ የዲሲ ምክር ቤት ተጠያቂነቱ ለዲሲ ነዋሪዎች ብቻ መሆኑን ለማረጋገጥ ኤድ ከንግድ ድርጅቶች፤ ከሕንጻ ገንቢዎች፤ ወይመ ከፍተኛ ገንዘብ ከሚሰጡ ለጋሾች ገንዘብ ላለመቀበል ቃል ገብቷል፡፡

ኤድ ብሩክላንድ ውስጥ ከቤተሰቡ ጋር

ቤተሰቦቻችን ዲሲ ውስጥ እንዲቆዩ መርዳት

እኔ እና ቤተሰቤ ላለፉት 30 ዓመታት እዚህ ከተማ ውስጥ ስለኖርን ዕድለኞች እንደሆን ይሰማናል፤ ዲሲ ውስጥ መፈናቀልን ለማቆም እና አቅም የሚፈቅድ ቤቶች እንዲሰሩ ለማድረግ ብቻ ሳይሆን ለሌሎች ከተሞችም ምሳሌ ለመሆን ከማንኛውም ጊዜ በተሻለ ሁኔታ ዛሬ አቅሙ አለን፤ ማንንም ወደ ሃላ ሳንጥል ወይም ወደ ጎን ሳንገፋ ወደ ፊት ለመጞዝ የሚያስፈልገን ነገር ቢኖር ምክር ቤት ውስጥ አዲስ አመራር መፍጠር ነው፡፡

ኤድ ብሩክላንድ ውስጥ ከቤተሰቡ ጋር

አርቆ አሳቢ ምክር ቤት ይኖረን ዘንድ ከእኛ ጎን ይቁሙ

ኤድ ሁሉም የዲሲ ነዋሪዎች የሚገባቸውን እና የሚፈልጉትን አይነት የከተማ አስተዳደር ይኖራቸው ዘንድ ለማስቻል ልምዱ አለው፤ ብዙ የቅንጅት አጋሮች ከጎኑ አሉ፤ በተጨማሪም ፍትህን ለመተግበር ቃል ገብቷል፤ ይህም እንዲሆን ከእኛ ጎን ይቁሙ፡፡

ከእኛ ጎን ይቁሙ

ወደፊት የታቀዱ ዝግጆቶችን እንድናሳውቅዎ፤ በጎ ፈቃድ እርዳታዎን እንዲለግሱ፤ እና እንዴት ለውጥ ማምጣት እንደምንችል ያሳውቁን ዘንድ እባክዎትን አድራሻዎን ይስጡን፤

ይለግሱ

ኤድ ከንግድ ድርጅቶች እና ልዩ ጥቅም ከሚሹ የሚቀበለው ቢኖር $0 ዶላር ነው፤ ውድድሩን የሚያንቀሳቅሰው ከማህበረሰቡ በሚያገኘው ልገሳ ይሆናል፤ የቻሉትን ያህል በመለገስ የእኛ እንቅስቃሴ አካል ይሁኑ፤ 1 የዲሲ ነዋሪዎች የሚለግሱትን 5 እጥፍ አድርጎ የዲሲ አዲስ የሕዝብ ፋይናንስ ፕሮግራም ይለግሳል!

1986

የከፍተኛ ስኬት መርሃ ግብር ላይ ለመሳተፍ ኤድ ወደ ዲሲ መጣ

1992

ኤድ እና ሚስቱ ሱዛን ብሩክላንድ ውስጥ ቤት ገዙ

1997

ኤድ እና ሱዛን ትልቁ ልጃቸውን ወደ ዲሲ የሕዝብ ትምህርት ቤት ላኩ

1989

የባጀት እና የፓሊሲ ማዕከል ቅድሚያ ለየትኞቹ ጉዳዮች መሰጠት እንዳለበት ለማስገንዘብ፤ በተለይ ደግሞ ለድሆች በመቆርቆር ኤድ የሂሳብ ትምህርቱን እና ችሎታውን ሥራ ላይ ማዋል ጀመረ

2001

የዲሲ መንግስት ገብያቸው አነስተኛ ለሆነ እና ሰርተው ለሚተዳደሩ ነዋሪዎች ቀልጣፋ ግልጋሎት ያቀርብ ያስችለው ዘንድ የዲሲ የፊስካል ፓሊሲ ተቋምን (DCFPI) ኤድ እንዲመሰረት አስቻለ

2016

የዲሲ ቤተሰቦች ከሥራ እረፍት ሲወጡ ክፍያ እንዲያገኙ እናም የዲሲ ምክር ቤት ሕግ አድርጎ እንዲያጸድቀው ኤድ የ DCFPI ዳይሪክተር ሆኖ ባገለገለብት ወቅት ከመራቸው ትግሎች አንደኛው ነው

2020

ለሁሉም የከተማ ነዋሪዎች ዕኩል ግልጋሎት የሚሰጥ ከተማ ለመገንባት ኤድ ለዲሲ ምክር ቤት መወዳደሩን ይፋ አደረገ

ለዲሲ ነዋሪዎች መታገል እና ማሸነፍ

ኤድ፤ ከታች ለተዘረዘሩት ጉዳዮች በስክታማ ሁኔታ ሲመራ ወይም አጋር ሆኖ ሲታገል ነው የቆየው፤

የኤድ ራዕይ ለዲሲ

ኤድ ላዛረ የዲሲ አጠቃላይ ምክር ቤት አባል ለመሆን እየተወዳደረ ያለው የከተማችን አጀንዳ ላይ የዘር ዕኩልነት እና የኢኮኖም ፍትህ ከፍተኛውን ቦታ ይዘው እንዲቆይ ለማድረግ ነው

ዕኩልነት ትምህርት ላይ

እያንዳንዱ የዲሲ ትምህርት ቤት—በተለይ ደግሞ በየሠፈራችን ያሉ የሕዝብ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ያብቡ ዘንድ የሚያስፈልገው ሁሉ እንዲቀርብ፤ ባሁኑ ጊዜ በቂ ሀብት ያለበት ማህበረሰብ ጋ ያሉ ትምህርት ቤቶች እየተንቀሳቀሱ ያሉት በተቀዳሚነት ስለሆን፤ ዲሲ ውስጥ ለሕዝብ ትምህርት ቤቶቹ የሚፈሰው መዋለ ንዋይ ዕኩል መሆን ብቻ ሳይሆን ተፎካካሪ መሆኑንም ለማረጋገጥ፡፡

የትምህርት ፋይናንስ ኮሚሽን ሊቀመንበር በነበርኩበት ወቅት፤ ድህነት የተስፋፋባቸው ትምህርት ቤቶች ተጨማሪ ሀብት ያገኙ ዘንድ ታግዬ ውጤት አስመዝግቤአልሁ፤ የምክር ቤት አባል ሆኜ ስመረጥ ይህንኑን ተግባሬን እቀጥልበታለሁ፤ ለትምህርት የምናወጥው ወጪ ለሁሉም ዕኩል መዳረሱን እንዲረጋገጥ በጥንቃቄ እሠራለሁ እናም የትምህርት ቤቶች አስተዳዳሪዎች ገንዘብ ለማን እንደሚሰጥ በሚወስኑበት ወቅት ተጠያቂ ሆነው እንዲቆዩ አደርጋለሁ፤ ለሁሉም ቤተሰቦች ልጆቻቸውን አቅም በሚፈቅድ እና ጥራቱ ከፍተኛ በሆነ የሕጻናት ቅድም ትምህርት ይልኩ ዘንድ እታገላለሁ፤ እንዲሁም አዋቂዎች ሥልጠና በሚቀበሉበት ጊዜ የተሻለ ትምህርት እንዲያገኙ፤ ልጆች ለሚያሳድጉ ቤተሰቦች ዋንኛ እና ቅድሚያ የሚሰጠው ቢኖር የኢኮኖሚ ፍትህ ሲሆን ለዚህም መታገሌን እቀጥላለሁ፡፡

መኖሪያ ቤት የሰብዓዊ መብት ነው

ዲሲ በአሁኑ ጊዜ አቅም የሚፈቅድ ቤት ቀውስ ውስጥ ነች፡ ባለፉት ሁለት አስርተ ዓመታት ሠፈሮች እና ማህበረሰቦች ተፈናቅለዋል፤ የቤት ዋጋ መናር ማንንም ከቤቱ እና ከከተማው ማፈናቀል የለበትም፡፡

እንደ አንድ ምክር ቤት አባልነቴ የዲሲ ከተማ አቅም ለሚፈቅድ ቤት የሚያውለውን መዋለ ንዋይ እጥፍ እንዲያደርግ እታገላለሁ፤ እፈናቀል ይሆን ብሎ ለሚሰጋ ለእያንዳንዱ ቤተሰብ በሚቀጥሉት አስርተ ዓመታት አቅም የሚፈቅድ መኖሪያ ለመገንባት ቃል መግባት አለብን፤ የዲሲ መሪዎች ይህን ለመፈጸም ምን ማድረግ እንዳለባቸው ያውቃሉ፤ ግን እስከ ዛሬ ድረስ ገንዘብ አልመደቡለትም፡፡

ለሁሉም የሚሠራ ኢኮኖሚ

እያንዳንዱ ዲሲ ውስጥ የሚሰራ ሠራተኛ ተገቢ እና ሊያኖረው የሚችል ክፍያ ማግኘት ይገባዋል፤ እንዲሁም ሥራ የሚፈልግ ማንኛውም ነዋሪ ሥራ ማግኘት መቻል ይኖርበታል፤ በፈረቃ የሚሰሩ ሠራተኞች ፍትሃዊ የሥራ ሰዓታት እንዲኖራቸው እናም በፈለጉ ጊዜ ሙሉ ሰዓት ሠራተኛ መሆን መቻል ይኖርባቸዋል፤ ተባራሪ ሠራተኛች ቢያንስ የተመደበውን አነስተኛ ክፍያ ማግኘት ይኖርባቸዋል፤ የእኛ መንግሥት ሰፊ ፕሮጀክቶችን በሚጀምርበት ወቅት ለግንባታ ሠራተኞች እንዲሁም ለቋሚ ሠራተኞች የሚፈጠረው ሥራ ጥራቱ ከፍተኛ የሆነ እና ጥቅማ ጥቅሞቹ ደረጃ የጠበቁ መሆን ይኖርበታል፤ አስተማሪዎች በዲሲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶችም ሆነ በቻርተር ትምህርት ቤቶች ያሉ ፍትሃዊ ክፍያ ማግኘታቸውን ማረጋገጥ አለብን፤ እንደ አንድ ምክር ቤት አባልነቴ የዲሲ ኢኮኖሚ ፍትሃዊ እንዲሆን እና በከተማችን ላሉ ሰርቶ አደር ቤተሰቦች መታገሌን እቀጥላለሁ፡፡ 

ፍትሃዊ የጤና እንክብካቤ

የአመጽ ተጽዕኖ የተጠቁት ሠፈሮቻችን የድንገተኛ አደጋ ሕክምና ማዕከል የላቸውም፤ በአሁኑ ጊዜ በሩን ክፍት አድርጎ ያለው ብቸኛ ሐኪም ቤትም የሚያስፈልገው አቅርቦት አልተሞላለትም፤ በከተማችን ጥቁር ሴቶች በወሊድ ጊዜ የመሞት እድላቸው ከማንኛቸውም የአገሪቷ ግዛቶች ጋር ሲነጻጸር መጠኑ ከፍ ያለ ነው፤ የጤና እንክብካቤ በከፍተኛ ደረጃ ለሚያስፈልጋቸው በጣም አስቸጋሪ እያደረግንባቸው ነው፤ እያንዳንዱ ሠፈር ውስጥ እና ማህበረሰብ ውስጥ ያሉ ነዋሪዎቻችንን ጤና መንከባከብ አለብን፤ እንደ ምክር ቤት አባልነቴ፤ በዲሲ ያለውን የጤና እንክብካቤ ክፍተት ለመቅረፍ እና እያንዳንዱ ነዋሪ፤ ዘሩ ወይም ገቢው እንቅፋት ሳይሆንበት የሚያስፈልገውን የጤና እንክብካቤ ያገኝ ዘንድ እታገላለሁ፡፡

ከኛ እሴቶች ጋር የሚስማማ የሞራል በጀት

የዲሲ ምክር ቤት የረጅም ጊዜው ታሪኩ እንደሚያሳየን የሚያጞጉ ፕሮግራሞችን እና ፓሊሲዎችን ያቀርባል — ከዛ በኋላ ግን ወጪ አይመድብላቸውም ወየም እንዲተገበሩ አያደርግም፤ ይህ መቀየር አለበት፡፡

ቅድሚያ የምንሰጣቸውን ጉዳዮችን እውን የምናደርጋቸው በባጀት አመደባበባችን ሲሆን ፤ የምንተማመንበት ከተማ ይኖረን ዘንድ ገቢያችንን እንዴት ለእኛ ጥቅም ላይ እንዲውል የሚያስችል የምክር ቤት አባል የሚያስፈልገን ጊዜው አሁን ነው፤ ባጀት የመደብንላቸው ፕሮግራሞች የብዙሃኑ የዲሲ ቤተሰቦች ፍላጎት ማንጸባረቃቸውን ለማረጋገጥ ቁርጠኛ የበላይ ክትትል የሚያስፈልግበት ጊዜ አሁን ነው፤ያለፉትን ሁለት አሥርተ ዓመታት ያሳለፍኩት የከተማው ባጀት የተሻለ፤ ዕኩልነቱን የጠበቀ፤ እና ውጤታማ እንዲሆን ለማስቻል ነበር፤ የምክር ቤት አባል በምሆንበት ጊዜ ልምዴን ሥራ ላይ በማዋል ቀዳዳዎቹን እደፍናለሁ፤ ፍሬ የሌላቸውን ድጎማዎችን አስወግዳለሁ፤ እና የሁሉንም የከተማ ነዋሪዎች ችግሮችን የሚያስተናግዱ ፕሮግራሞች እፈጥራለሁ፡፡

Join the Family!

Sign Up for Emails From Ed